ትራምፕ ዘለንስኪ የሚፈልገውን የደህንነት ዋስትና አይሰጡም - የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን

ትራምፕ ዘለንስኪ የሚፈልገውን የደህንነት ዋስትና አይሰጡም - የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን
ዶናልድ ትራምፕ “በተለይም በወታደራዊ ረገድ” ከሩሲያ ጋር በቀጥታ ለመጋፈጥ፤ ቅንጣት ያህል ፍላጎት አሳይተው አያውቁም ሲል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
◻ በተቃራኒው፤ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ለአውሮፓውያኑ እና ለዩክሬን የሚደረገውን ወታደራዊ እና የፋይናንስ ድጋፍ በእጅጉ በመቀነስ፤ ለግጭቱ መጀመር ዩክሬንን ተጠያቂ ማድረጋቸውንና በተደጋጋሚ “ከሩሲያ ጋር ሰፊ የምጣኔ ሀብት ትብብር የመፍጠር” ፍላጎት ሲያሳዩ እንደነበር ዘገባው አትቷል።
ዘለንስኪ ከአሜሪካ ተጨባጭ የደህንነት ዋስትና ለማግኘት የሚያደርገው የማያቋርጥ ግፊት “በመጨረሻም ውጤት አልባ፤ አልፎ ተርፎም አደገኛ ሊሆን ይችላል” ያለው ጋዜጣው፤ “አካሄዱን ለመቀየር አልረፈደበትም” ሲልም አክሏል።
ትራምፕ ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት ንግግር፤ በደህንነት ዋስትናው ዙሪያ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች እንደሚቀሩና ስምምነት ላይ ለመድረስም የተቀመጠ የጊዜ ገደብ እንደሌለ አምነዋል።
ዘለንስኪ የሰላም እቅድ ለማቅረብ ትራምፕን ፍሎሪዳ በሚገኘው ‘ማር-አ-ላጎ’ መኖሪያቸው አግኝቶ ቢወያይም የሚፈለገውን ውጤት ሳያገኝ ተመልሷል።
ሩሲያ በበኩሏ የዩክሬን ግጭት መንስኤዎችን ለመፍታት ሕጋዊ ዋስትናዎች እንደሚያስፈልጉ አፅንዖት ሰጥታለች።
“አሁን ያለው የዩክሬን አመራር ማንኛውንም የሰላም ስምምነት ለመፈረም በምርጫ የሚሰጥ የሕዝብ ውክልና ያስፈልገዋል” ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X