“የኢትዮጵያን ቅርስ ያልያዘ የአውሮፓ ሀገር የለም” - የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“የኢትዮጵያን ቅርስ ያልያዘ የአውሮፓ ሀገር የለም” - የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ
“የኢትዮጵያን ቅርስ ያልያዘ የአውሮፓ ሀገር የለም” - የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.01.2026
ሰብስክራይብ

“የኢትዮጵያን ቅርስ ያልያዘ የአውሮፓ ሀገር የለም” - የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ

ሀገሪቱን በተለያየ ግዜ እና ምክንያት የረገጡ አውሮፓውያን ባዶ እጃቸውን አልተመለሱም ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ የተናገሩት የኮሚቴው ዋና ጸሐፊ እና የታሪክ ተመራማሪው አባተ ጎበና (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች በዋናነት የሚገኙባቸው የአውሮፓ ሀገራት ብሪታኒያ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ እንደሆኑ ምሁሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

“አብዛኛዎቹ ቅርሶች፣ ጽሑፎች፣ ዕቃዎች፣ ቅዱሳዊና ንጉሣዊ ቅርሶች በአብዛኛው በብሪታንያ ነው የሚገኙት። ነገር ግን በጣሊያን፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ስብስቦች አሉ። ምንም አይነት የኢትዮጵያ ቅርስ የሌለበት የአውሮፓ ሀገር የለም ማለት እንችላለን። በብሪታንያ በሺዎች የሚቆጠሩ የእጅ ጽሑፎችና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቅርሶች አሉ። ወደ ጣሊያን ስንሄድ በሁለቱ ወረራዎች ወቅት በኃይል ወይም በሌሎች በርካታ መንገዶች ብዙ ነገሮች ተወስደዋል።”

እነዚህን የኢትዮጵያ ቅርሶች ለማስመልስ ቅንጅት እና የሀገራቱን ሕጎች በአግባቡ መረዳት እንደሚገባም ነው ባለሙያው ያሳሰቡት፡፡

“ሀገራቱ በተዘረፉ እና በሙዚየሞቻቸው ባከማቿቸው ቅርሶች ዙሪያ ያራሳቸው ሕጎች አሏቸው። ስለዚህ እነዚህን የተለያዩ ሕጎች ማወቅ ይገባል። እንደ ሀገራቱ ሁኔታ የተለያዩ ደንቦች አሉ እና ኮሚቴው (ቅርስ አስመላሽ) እነዚህን የተለያዩ ደንቦች ማወቅ እና ቅድመ ሁኔታዎቹን ለማሟላት ስትራቴጂ ሊኖረው ይገባል።”

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0