በአዲስ ዓመት ዋዜማ በካፌ ላይ ተፈጽሞ ህይወት በቀጠፈው ጥቃት፤ ኪዬቭ ሦስት ድሮኖችን እንደተጠቀመች የሄርሶን አስተዳዳሪ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ ዓመት ዋዜማ በካፌ ላይ ተፈጽሞ ህይወት በቀጠፈው ጥቃት፤ ኪዬቭ ሦስት ድሮኖችን እንደተጠቀመች የሄርሶን አስተዳዳሪ ገለጹ
በአዲስ ዓመት ዋዜማ በካፌ ላይ ተፈጽሞ ህይወት በቀጠፈው ጥቃት፤ ኪዬቭ ሦስት ድሮኖችን እንደተጠቀመች የሄርሶን አስተዳዳሪ ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.01.2026
ሰብስክራይብ

በአዲስ ዓመት ዋዜማ በካፌ ላይ ተፈጽሞ ህይወት በቀጠፈው ጥቃት፤ ኪዬቭ ሦስት ድሮኖችን እንደተጠቀመች የሄርሶን አስተዳዳሪ ገለጹ

የመጀመሪያው ድሮን በሞስኮ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ሌሊት ከመሆኑ አሥር ደቂቃ በፊት መድረሱን የሄርሶን ክልል አስተዳዳሪ ቭላድሚር ሳልዶ ለሩሲያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጸዋል። ድሮኑ በአቅራቢያው ቢያርፍም ፍንጣሪው ካፌው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አላደረሰም ብለዋል።

በመቀጠል ሁለተኛው ድሮን ቦታው ላይ አርፏል። ሳልዶ፤ ድሮኑ የተሸከመው 20 ኪሎ ግራም የቲ.ኤን.ቲ ፈንጂ “ለአንዲት ትንሽ ካፌ እጅግ ከፍተኛ ነው” ብለዋል።

ከደቂቃዎች በኋላ ሰዎች ከካፌው መሸሽ ሲጀምሩ፤ ሦስተኛው ድሮን ሌላ ጥቃት ፈጽሟል።

“ይህ እጅግ በጭካኔ እና በፋሽስታዊ መንገድ የታቀደ ድርጊት ነው” ሲሉ ሳልዶ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

በጥቃቱ የሞቱ ንጹሃን ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን እስከ ዛሬ አርብ ድረስ በትንሹ ሁለት ታዳጊዎችን ጨምሮ 27 ሰዎች ተገድለዋል። ከ50 በላይ ሰዎች ሲቆስሉ 31 ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል። ድርጊቱን በሽብርተኝነት የፈረጁት ባለሥልጣናት፤ የወንጀል ምርመራ ከፍተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0