በኢራን የኒውክሌር መርኃ-ግብር ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻል የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ
17:02 02.01.2026 (የተሻሻለ: 17:04 02.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢራን የኒውክሌር መርኃ-ግብር ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻል የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ
በኢራን የኒውክሌር መርኃ-ግብር ዙሪያ ለተፈጠረው አለመግባባት ሁሉም ወገኖች በቂ የፖለቲካ ፍላጎት ካሳዩ መፍትሄ ማግኘት እንደሚቻል አንድ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
“ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አስፈላጊው የፖለቲካ ቁርጠኝነት ካለ፤ በኢራን የኒውክሌር መርኃ-ግብር ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ ሙሉ በሙሉ የሚቻል ነው ብለን እናምናለን። በዚህ ረገድ የሚመዘገብ ማንኛውም መሻሻል የምንቀበልው ነው” ሲሉ በሚኒስቴሩ የኒውክሌር መሣሪያ እና የጦር መሣሪያ ቁጥጥር መምሪያ ዳይሬክተር ኦሌግ ፖስትኒኮቭ ተናግረዋል።
ሩሲያ፤ ኢራን በኒውክሌር መሣሪያ ቁጥጥር ስምምነት እንዲሁም ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በገባችው አጠቃላይ የመከላከያ ስምምነት መሠረት ግዴታዎቿን እየተወጣች መሆኑን እንደምታውቅ አክለዋል።
ፖስትኒኮቭ ቀደም ሲል ባለፈው ዓመት ያልተሳኩ ድርድሮችን በመጥቀስ፤ የምዕራባውያን ሀገራት ሆን ብለው በኢራን የኒውክሌር መርኃ-ግብር ዙሪያ መሻሻል እንዳይኖር ዝግ ፖሊሲ ይከተላሉ በማለት ተችተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X