የናይጄሪያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የ26.3 በመቶ ጭማሪ አሳየ
15:21 02.01.2026 (የተሻሻለ: 15:24 02.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የ26.3 በመቶ ጭማሪ አሳየ
ሀገሪቱ በ2025 ሦስተኛው ሩብ ዓመት በአጠቃላይ 720 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏን የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል።
ይህ አሃዝ ከ2024 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጉልህ ጭማሪ የሚያሳይ ሲሆን ከ2025 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ጋር ደግሞ የ700 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።
የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ ለዚህ እድገት እንደ ምክንያት የጠቀሳቸው፦
◻ የባለሀብቶች እምነት መጨመር፣
◻ በሀገሪቱ የፋይናንስ ገበያ ቀጣይነት ያለው የውጭ ዜጎች ተሳትፎ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀገሪቱ የክፍያ ሚዛን፤ የወቅቱን የ3.42 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ሂሳብ ትርፍ ጨምሮ 4.6 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ትርፍ አስመዝግቧል፡፡
የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ8.45 ቢሊዮን ዶላር የድፍድፍ ነዳጅ የወጪ ንግድ እና የተጣራ ነዳጅ ገቢ ንግድ ቅናሽ ምክንያት በሰኔ ወር ከነበረበት 37.81 ቢሊዮን ዶላር፤ በመስከረም ወር መጨረሻ ወደ 42.77 ቢሊዮን ዶላር አድጓል።
እነዚህ አመልካቾች ናይጄሪያ ለዓመታት ከቆየው ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት እና ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ ስጋት ወጥታ ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ማገገም ምዕራፍ እየተሸጋገረች መሆኑን ያሳያሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X