ከ2 ሚሊዮን በላይ የባንክ ሂሳቦች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር መተሳሰራቸው ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከ2 ሚሊዮን በላይ የባንክ ሂሳቦች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር መተሳሰራቸው ተገለፀ
ከ2 ሚሊዮን በላይ የባንክ ሂሳቦች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር መተሳሰራቸው ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.01.2026
ሰብስክራይብ

ከ2 ሚሊዮን በላይ የባንክ ሂሳቦች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር መተሳሰራቸው ተገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ባንኮች ደንበኞቻቸውን ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በቀን እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ የማረጋገጫ ሂደቶች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት አገናኝ የሆነው ኢትስዊችን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ በ2022 ዓ.ም የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂን ለማሳካት በምታደርገው ጥረት፤ እስካሁን 30 ሚሊዮን ዜጎች ለፋይዳ የተመዘገቡ ሲሆን በ2019 ዓ.ም መጨረሻ ይህንን ቁጥር ወደ 70 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዷል።

ብሔራዊ ባንክ ሁሉም 31 የንግድ ባንኮች ከቆየው የቴክኖሎጂ ሥርዓት ወደ ዘመናዊው የኤሌክትሮኒክ ደንበኛ ማረጋገጫ እንዲሸጋገሩ ኅዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ መመሪያ ማውጣቱ ይታወቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0