በጦርነት ለተጎዱ የጋዛ ህፃናት የቨርቹዋል ሪያሊቲ ሕክምና ‘ከጭንቀት ማምለጫ’ እየሆነላቸው ነው ተባለ

ሰብስክራይብ

በጦርነት ለተጎዱ የጋዛ ህፃናት የቨርቹዋል ሪያሊቲ ሕክምና ‘ከጭንቀት ማምለጫ’ እየሆነላቸው ነው ተባለ

በጋዛ፤ የእስራኤል ጦርነት ባደረሰው የከፋ ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ የተጎዱ ህፃናት፤ ምናባዊ እውነታ ቴክኖሎጂ ጭንቀታቸውን እንዲቋቋሙ እያገዘ ነው።

የቴክኖሎጂው አልሚ በከር ሳሌም ለስፑትኒክ እንደገለጹት፤ ይህ የህክምና ዘዴ ህፃናቱን በምናባቸው ወደ ሰላማዊ ደኖች፣ አትክልት ስፍራዎች እና የተፈጥሮ አካባቢዎች በመውሰድ፤ ከጦርነቱ ፍርስራሽ እና አስከፊ ትዝታዎች ለተወሰነ ጊዜ እንዲርቁ ያደርጋቸዋል።

አንድ ህፃን ለስፑትኒክ በሰጠው አስተያየት፤ "ጦርነቱን ለጥቂት ጊዜ እንድረሳ አድርጎኛል። ለረጅም ጊዜ ተሰምቶኝ የማያውቅ ደስታ ተሰምቶኛል" ብሏል።

እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ፤ ትዕይንቶቹ በሥነ-ልቦና ጥናቶች ላይ ተመስርተው የተሠሩ በመሆናቸው ፍርሃትንና ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳሉ።

አንዲት እናት ልጃቸው ከህክምናው በኋላ በድጋሚ መጫወት መጀመሩን ገልጸዋል። ሆኖም የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች እና ሌሎች ግብዓቶች እጥረት የፕሮግራሙን ተደራሽነት እንደገደቡ አልሚዎቹ ጠቁመዋል።

እንደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ከሆነ፤ በጋዛ ከሚገኙ አንድ ሚሊዮን ህፃናት መካከል ወደ 90 በመቶ የሚጠጉት በከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ ከ20 ሺህ በላይ ህፃናት ሲገደሉ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል አልያም ወላጅ አልባ ሆነዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በጦርነት ለተጎዱ የጋዛ ህፃናት የቨርቹዋል ሪያሊቲ ሕክምና ‘ከጭንቀት ማምለጫ’ እየሆነላቸው ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ
1/4
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በጦርነት ለተጎዱ የጋዛ ህፃናት የቨርቹዋል ሪያሊቲ ሕክምና ‘ከጭንቀት ማምለጫ’ እየሆነላቸው ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ
2/4
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በጦርነት ለተጎዱ የጋዛ ህፃናት የቨርቹዋል ሪያሊቲ ሕክምና ‘ከጭንቀት ማምለጫ’ እየሆነላቸው ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ
3/4
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በጦርነት ለተጎዱ የጋዛ ህፃናት የቨርቹዋል ሪያሊቲ ሕክምና ‘ከጭንቀት ማምለጫ’ እየሆነላቸው ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ
4/4
1/4
2/4
3/4
4/4
አዳዲስ ዜናዎች
0