ጋናዊው ‘የጥፋት ቀን 'ነቢይ’ የሕዝብን ሰላም በሚያሸብሩ የሳይበር እንቅስቃሴዎች ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጋናዊው ‘የጥፋት ቀን 'ነቢይ’ የሕዝብን ሰላም በሚያሸብሩ የሳይበር እንቅስቃሴዎች ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ
ጋናዊው ‘የጥፋት ቀን 'ነቢይ’ የሕዝብን ሰላም በሚያሸብሩ የሳይበር እንቅስቃሴዎች ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.01.2026
ሰብስክራይብ

ጋናዊው ‘የጥፋት ቀን 'ነቢይ’ የሕዝብን ሰላም በሚያሸብሩ የሳይበር እንቅስቃሴዎች ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ

ኢቦ ኖህ በሚል ቅጽል ስሙ በስፋት የሚታወቀውና ራሱን ‘ነቢይ’ ብሎ የሚጠራው ኢቫንስ እሹን፤ በሕዝብ ዘንድ ስጋትና ሁከትን ሊፈጥሩ በሚችሉ የበየነ መረብ ይዘቶች በሳይበር ወንጀል ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።

ይህም የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ከዘመን መለወጫ ዋዜማ ጋር ተያይዞ የጥፋት ቀን ትንቢቶችን በሚያሠራጩ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ በሰጡ ማግስት የመጣ ነው።

ኢቦ ኖህ እ.ኤ.አ ታህሳስ 25 ቀን ዓለምን የሚያጠፋ የጎርፍ መቅሰፍት ይከሰታል በሚል "ትንቢት" በመጥፎም ቢሆን እውቅናን አግኝቶ ነበር። መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው በማለት አንድ ትልቅ የእንጨት መርከብ የሠራ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በጸሎት አማካኝነት በደረሰኝ "አዲስ ራዕይ" ጥፋቱ ተራዝሟል ሲል መግለጫ ሰጥቷል።

የጋና ፖሊስ ለጊዜው የተመሠረተበትን ዝርዝር ክስ ይፋ ባያደርግም፤ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያይዘ ሌላ የሚፈለግ ግለሰብ አለመኖሩም ታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0