የኪዬቭ የሩሲያ ክልሎችን የማጥቃት ሙከራ የዩክሬን ሠራዊት በጦር አውድማው የሚደርስበትን ሽንፈት የመሸፈን ዓላማ አለው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
18:27 01.01.2026 (የተሻሻለ: 18:34 01.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኪዬቭ የሩሲያ ክልሎችን የማጥቃት ሙከራ የዩክሬን ሠራዊት በጦር አውድማው የሚደርስበትን ሽንፈት የመሸፈን ዓላማ አለው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የዩክሬን ጦር በሄርሶን ክልል ስለፈጸመው ጥቃት ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጡ ቁልፍ መግለጫዎች፦
የሩሲያን ወታደራዊ ድሎች መቋቋም ያልቻለው እና የፑቲንን መኖሪያ ቤት ለመምታት ያደረገው ሙከራ ያልተሳካለት የኪዬቭ ወራሪ ኃይል፤ መከላከያ በሌላቸው ሲቪሎች ላይ ኃይሉን ማሳረፍ መርጧል።
ሩሲያ ኃላፊነት የሚሰማቸው ሉዓላዊ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ አካላት ይህንን ደም አፍሳሽ የሽብር ተግባር እንዲያወግዙ ታሳስባለች።
የኪዬቭ ስብስብ በሄርሶን ክልል የፈጸመው ጭፍጨፋ ዩክሬንን በገንዘብ በሚደግፉ የምዕራባውያን ሀገራት ሕሊና ላይ ያርፋል።
ይህንን አሳዛኝ ድርጊት ችላ የሚሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኒዮ-ናዚ የሽብር ጥቃቶች ተባባሪ ይሆናሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X