የቡርኪና ፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ የኢምፔሪያሊስቶች ስሁት መረጃ ስርጭቶችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት አደነቁ
የቡርኪና ፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ የኢምፔሪያሊስቶች ስሁት መረጃ ስርጭቶችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት አደነቁ
ፕሬዚዳንቱ በመንግሥት እና በግል ኮሙኒኬሽን ዘርፍ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሠሩ አካላት "የኢምፔሪያሊስት ፕሮፓጋንዳ እና የተሳሳቱ መረጃዎችን" በመዋጋት ወሳኝ አጋሮች እንደሆኑ በመግለፅ እውቅና ሰጥተዋል።
ትራኦሬ፤ የእነዚህ አካላት ጥረት ስለ ሀገሪቱ ትክክለኛ እና አዎንታዊ ምሥል ለመገንባት እንደሚረዳ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ካስተላለፉት የዘመን መለወጫ መልዕክት የተወሰዱ ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦
◻ የቡርኪና ፋሶ ዲፕሎማሲ አሁን ካለው የጂኦ-ፖለቲካ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ይሆናል፤ ሀገሪቱም ሉዓላዊነቷን፣ ነፃነቷን እና ክብሯን ለሚያከብሩ አጋሮች በሯ ክፍት ነው።
◻ የሀገሪቱ መሪ የሳኅል ሀገራት ጥምረት ሊቀምንበርነት ተልዕኳቸውን እንዲወጡ የቡርኪና ፋሶ ሕዝብ እንዲደግፋቸው ጥሪ አቅርበዋል።
◻ በአራት ክልሎች የመንገድ ግንባታ ግብረ-ኃይሎች የተቋቋሙ ሲሆን በ2026 ብሔራዊ፣ ክልላዊ እና የአውራ ጎዳና መንገዶችን ለመገንባት አራት ተጨማሪ ክልሎች አስፈላጊው መሣሪያ ይሟላላቸዋል።
◻ ዘመናዊ የከተማ ፕላን ትኩረቱን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ እና ንፁህ ከተሞች ላይ ያደርጋል።
◻ በ2025 በግብርና፣ በእንስሳት እርባታ እና በዓሣ እርባታ ዘርፎች መሻሻል የታየ ሲሆን በጥሩ የዝናብ ስርጭት እና በገጠሩ ማኅበረሰብ ንቁ ተሳትፎ በምግብ ራስን የመቻል አቅም ተረጋግጧል።
◻ በ2026 አዳዲስ የግብርና ማሽነሪዎችን በማቅረብ፣ በነፃ ወይም በከፍተኛ ድጎማ የእርሻ ሥራዎችን በማከናወን እና ጥራት ያላቸው ምርጥ ዘሮችን በማቅረብ ጥረቶቹ ይቀጥላሉ።
◻ በፀጥታ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢነርጂ እና በማዕድን ዘርፎች የታዩ መሻሻሎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X