የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎች የዓለም መሪዎች ለሱዳን 70ኛ የነጻነት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎች የዓለም መሪዎች ለሱዳን 70ኛ የነጻነት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎች የዓለም መሪዎች ለሱዳን 70ኛ የነጻነት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.01.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎች የዓለም መሪዎች ለሱዳን 70ኛ የነጻነት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ፑቲን፤ የሀገሪቱን 70ኛ ዓመት የነጻነት በዓል አስመልክቶ ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መላካቸውን የሱዳን ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የግብጹ አብደል ፋታህ አል-ሲሲ፣ የሞሮኮው ንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ፣ የሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሰልማን፣ የሶማሊያው ሐሰን ሼክ መሐሙድ እና የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋንን ጨምሮ ሌሎች የዓለም መሪዎችም ለአል-ቡርሃን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፑቲን እና አል-ቡርሃን ለመጨረሻ ጊዜ በአካል የተገናኙት እ.አ.አ በ2019 በሶቺ ከተካሄደው የመጀመሪያው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ባካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይት ወቅት ነበር። የሱዳኑ መሪ አስቀድሞ በጥቅምት 2025 ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው እና በመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ በተላለፈው የሩሲያ-አረብ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0