የአገው ፈረስ ባሕልን በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ቅድመ ሥራዎች መጠናቀቃቸው ተገለፀ
16:22 01.01.2026 (የተሻሻለ: 16:24 01.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአገው ፈረስ ባሕልን በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ቅድመ ሥራዎች መጠናቀቃቸው ተገለፀ
ባሕላዊ ቅርሱ ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት እንዲችል አስፈላጊ ሥራዎች ሲሠራ መቆየቱን እና በቀጣይ እውን ወደ ማድረግ እንደሚሸጋገር የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የአገው ፈረስ ባሕል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት መመዝገቡ የማኅበረሰቡን ተሳትፎ እና ማኅበራዊ መስተጋብር በማጎልበት በኩል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
86ኛው የአገው ፈረሰኞች ዓመታዊ በዓል በመጪው ጥር ወር ይከበራል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X