በኢትዮጵያ የአትሌቶች ባዮሎጂካል ፓስፖርት ላብራቶሪ ሊቋቋም ነው
15:50 01.01.2026 (የተሻሻለ: 15:54 01.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የአትሌቶች ባዮሎጂካል ፓስፖርት ላብራቶሪ ሊቋቋም ነው
የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ላብራቶሪ ለመገንባት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ላብራቶሪው አስፈላጊው መሠረተ ልማት ተሟልቶለት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የባለሥልጣኑ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አክሊሉ አዛዥ በበኩላቸው፤ ከዚህ ቀደም የምርመራ ሥራዎች በኳታር፣ በአውሮፓ ሀገራትና በኬንያ ይከናወኑ እንደነበር አስታውሰው፤ ላብራቶሪው በሀገር ውስጥ መቋቋሙ የውጭ ምንዛሬን የሚያድንና እንግልትን የሚያስቀር መሆኑን አስረድተዋል።
ላብራቶሪው ወደ ሥራ ሲገባ ከፀረ-አበረታች መድኃኒቶች ጋር በተያያዘ ጥብቅ መረጃዎችን ለማግኘትና ለሀገሪቱ አትሌቲክስ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X