ኒጀር ከ2023 እስከ 2025 የ6.5 በመቶ ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧ ተገለፀ
15:32 01.01.2026 (የተሻሻለ: 15:34 01.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኒጀር ከ2023 እስከ 2025 የ6.5 በመቶ ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧ ተገለፀ
ይህ ዕድገት የተገኘው በአዲስ የአጋርነት ስምምነቶች እና መንግሥት እንደ ማዕድን፣ ግብርና፣ ኢነርጂ እና ኢንዱስትሪ ባሉ ቁልፍ ዘርፎች ባከናወናቸው የልማት ሥራዎች መሆኑን የኒጀር ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ 2025 የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት እና ምርታማነት ለማጠናከር የታለሙ ተከታታይ ስልታዊ እርምጃዎች የታዩበት ነበር፦
በአንዳንድ ኩባንያዎች ውስጥ የሥራ መደቦችን በሀገር በቀል ባለሙያዎች በመተካት የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድልን ማሳደግ፣
የዶሶ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ቀጣይ ልማት፣
የምግብ ዋስትና እና የግብርና ምርትን ለማሳደግ፤ ሰፊ የመስኖ መርኃ-ግብር ትግበራ፣
የሀገር ውስጥ ምርቶችን መግዛትና እና ማስተዋወቅን የሚያበረታታ አዋጅ ማፅደቅ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X