የዚምባብዌ በወርቅ የሚደገፍ መገበያያ ገንዘብ በዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ መናር እና በውጭ ምንዛሬ ክምችት ማደግ ምክንያት መሻሻል አሳየ
18:02 31.12.2025 (የተሻሻለ: 18:04 31.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዚምባብዌ በወርቅ የሚደገፍ መገበያያ ገንዘብ በዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ መናር እና በውጭ ምንዛሬ ክምችት ማደግ ምክንያት መሻሻል አሳየ
የዚምባብዌ ማዕከላዊ ባንክ ረቡዕ ዕለት ባወጣው መረጃ መሠረት፤ ዚግ የተሰኘው የሀገሪቱ ገንዘብ ከዚህ ቀደም ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ያጣውን ዋጋ በመመለስ በአሁኑ ወቅት አንድ ዶላር በ25.98 ዚግ እየተመነዘረ ይገኛል። ይህም ገንዘቡ ካለፈው ጥር ወር ወዲህ ያስመዘገበው ጠንካራ የዋጋ ደረጃ ነው።
ገንዘቡ ሊያገግም የቻለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የወርቅ ዋጋ በመጨመሩ እና የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በማደጉ እንደሆነ ባንኩ አስታውቋል።
ዚግ፤ እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2024 ሥራ ላይ ከዋለ ጀምሮ በዚህ ዓመት ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ዋጋው የቀነሰው 0.7 በመቶ ብቻ ነው።
ይህ አንጻራዊ መረጋጋት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና በዶላር ጥገኝነት ስትታመስ ለቆየችው እና አስተማማኝ ብሔራዊ ገንዘብ ለመፍጠር ጥረት ለምታደርገው ዚምባብዌ፤ ትልቅ ስኬት ነው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X