በፑቲን መኖሪያ ላይ ‘በከፍተኛ የመንግሥት ደረጃ አረመኔያዊ የሽብር’ ጥቃት ተፈጽሟል - የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበፑቲን መኖሪያ ላይ ‘በከፍተኛ የመንግሥት ደረጃ አረመኔያዊ የሽብር’ ጥቃት ተፈጽሟል - የቤላሩስ ፕሬዚዳንት
በፑቲን መኖሪያ ላይ ‘በከፍተኛ የመንግሥት ደረጃ አረመኔያዊ የሽብር’ ጥቃት ተፈጽሟል - የቤላሩስ ፕሬዚዳንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.12.2025
ሰብስክራይብ

በፑቲን መኖሪያ ላይ ‘በከፍተኛ የመንግሥት ደረጃ አረመኔያዊ የሽብር’ ጥቃት ተፈጽሟል - የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

“ለመሆኑ ከዚህ ድርጊት ማን ነው የሚጠቀመው?” ሲሉ አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በኖቭጎሮድ ክልል በሩሲያ ፕሬዚዳንት መኖሪያ ላይ ዩክሬን በቅርቡ የፈጸመችውን የድሮን ጥቃት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

እንደ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገለጻ፤ የኪዬቭ አገዛዝ ሰኞ ምሽት 91 ድሮኖችን በመጠቀም በኖቭጎሮድ ክልል በሚገኘው የፑቲን መኖሪያ ላይ የሽብር ጥቃት ፈጽሟል።

ሁሉም ድሮኖች በአየር መከላከያ ሥርዓቶች በመውደማቸው የሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። ጥቃቱን ተከትሎ ሩሲያ በዩክሬን ቀውስ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ከምታደርገው ድርድር የመውጣት ፍላጎት ባይኖራትም የድርድር አቋሟ ግን በድጋሚ እንደሚታይ ላቭሮቭ አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0