የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለተቀናጁ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ፓርኮች የሚሆኑ 17 ስትራቴጂካዊ ቦታዎች መለየቱን አስታወቀ
15:51 31.12.2025 (የተሻሻለ: 15:54 31.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለተቀናጁ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ፓርኮች የሚሆኑ 17 ስትራቴጂካዊ ቦታዎች መለየቱን አስታወቀ
አዳዲሶቹ ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁትን የቡሬ፣ የቡልቡላ እና የይርጋለም የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ መለየታቸው ተጠቁሟል፡፡
መንግሥት ለአምራች ኢንዱስትሪው ልዩ ትኩረት በመስጠት ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ መሠረተ ልማቶችን እንዳሟላ ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢንቨስትመንት መድረክ ላይ አስታውቋል።
የፓርኮቹ መገንባት ዋነኛ ዓላማዎች፦
◻ እሴት በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ገቢን ማሳደግ፣
◻ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣
◻ የሀገር ውስጥ ገበያን ማስፋፋት፣
◻ የመንግሥት ገቢን ማሳደግ፡፡
ኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገች ያለችውን የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት በመጠቀም፤ የሀገር ውስጥ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትኩረት እንደምትሠራ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X