የጊኒ የሽግግር መንግሥት መሪ ማማዲ ዱምቡያ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ማሸነፋቸው ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጊኒ የሽግግር መንግሥት መሪ ማማዲ ዱምቡያ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ማሸነፋቸው ተገለፀ
የጊኒ የሽግግር መንግሥት መሪ ማማዲ ዱምቡያ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ማሸነፋቸው ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.12.2025
ሰብስክራይብ

የጊኒ የሽግግር መንግሥት መሪ ማማዲ ዱምቡያ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ማሸነፋቸው ተገለፀ

የጊኒ የምርጫ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ባወጣው ጊዜያዊ ውጤት መሠረት፤ ማማዲ ዱምቡያ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው 86.72 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫውን ውጤት አስመልክቶ የሚቀርቡ ሕጋዊ ቅሬታዎች ካሉ ተመልክቶ፤ በስምንት ቀናት ውስጥ የዱምቡያን ድል እንደሚያፀድቅ ተገልጿል።

በግምት 85 በመቶ የሚሆን የመራጮች ተሳትፎ የታየበት ይህ ምርጫ፤ እ.ኤ.አ በ2021 ከተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በኋላ ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር ሽግግር ማድረጓን የሚያበስር ይሆናል ተብሏል።

የመንግሥት ለውጡን የመሩት ዱምቡያ፤ በምርጫው ከሌሎች ስምንት ዕጩዎች ጋር የተወዳደሩ ሲሆን ድሉ ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት ሀገሪቱን መመራት የሚያስችል ሥልጣን ይሰጣቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0