ሶማሊያ ለየመን መንግሥት ድጋፏን ገለፀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሶማሊያ ለየመን መንግሥት ድጋፏን ገለፀች
ሶማሊያ ለየመን መንግሥት ድጋፏን ገለፀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.12.2025
ሰብስክራይብ

ሶማሊያ ለየመን መንግሥት ድጋፏን ገለፀች

ሞቃዲሾ ለየመን አንድነት፣ ለሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት እና ለግዛታዊ አንድነቷ ጠንካራ ድጋፏን በድጋሚ በማረጋገጥ፤ ማንኛውንም ዓይነት የውጭ ጣልቃ ገብነት ትቃወማለች ሲል የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።

መግለጫው፤ ሳዑዲ አረቢያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለየመን ተገንጣይ የደቡብ ሽግግር ምክር ቤት የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም እና ወታደሮቿን እንድታስወጣ በይፋ በጠየቀችበት ወቅት የተፈጠረውን ክልላዊ ውጥረት ተከትሎ የመጣ ነው።

የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር፤ ሳዑዲ አረቢያ ለቀጣናው መረጋጋት የምትጫወተውን "ቁልፍ ሚና" በማድነቅ፤ ለየመን ሕጋዊ መንግሥት እገዛ የሚያደርገውን ሳዑዲ መር ጥምረት እንደምትደግፍ ገልጻለች።

ሶማሊያ የየመን ደህንነት ከቀይ ባሕር እና ከአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለውም አፅንዖት ሰጥታለች።

በዚህም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለግጭቱ ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርባለች።

ቀደም ሲል በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚደገፉት የደቡብ ሽግግር ምክር ቤት ኃይሎች በምስራቅ የመን የሚገኙትን የሀድራማውት እና አል-ማህራ ግዛቶች ተቆጣጥረው ነበር። ይህንን ተከትሎም ፕሬዚዳንት አል-አሊሚ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር የነበራቸውን የመከላከያ ስምምነት በማቋረጥ የኤምሬት ወታደሮች እንዲወጡ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ለተገንጣይ ኃይሎች የተላከ የጦር መሳሪያ በሳዑዲ ጄቶች ማክሰኞ ዕለት መመታቱን ጠቅሰዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቀረበባትን ክስ በማስተባበል፤ ውጥረቱ እንዲረግብ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጻለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0