ቡርኪና ፋሶ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ሙሉ የቪዛ እገዳ ጣለች
14:30 31.12.2025 (የተሻሻለ: 14:34 31.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቡርኪና ፋሶ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ሙሉ የቪዛ እገዳ ጣለች
ይህ ውሳኔ አሜሪካ ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጥር 1 ቀን 2026 ጀምሮ ለቡርኪና ፋሶ ዜጎች ቪዛ መስጠት እንደምታቆም ይፋ ካደረገችበት የታኅሣሥ 7 ቀን ውሳኔ ጋር በቀጥታ የተያያዘ "አጸፋዊ እርምጃ" መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካራሞኮ ዣን ማሪ ትራኦሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የቡርኪና ፋሶ መንግሥት ይህንን እርምጃ የወሰደው በዓለም አቀፍ ግንኙነት፤ የሀገራት ሉዓላዊ እኩልነት እና የጋራ መከባበር መርህን መሠረት በማድረግ እንደሆነ ሚኒስቴሩ አብራርቷል።
መግለጫው አክሎም፤ ቡርኪና ፋሶ በጋራ ፍላጎቶች እና መከባበር ላይ ለተመሠረቱ የትብብር አጋርነቶች ሁልጊዜም ዝግጁ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X