ቡናን ለምግብና መጠጥ ቱሪዝም ልማት ለመጠቀም እየሠራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ
14:00 31.12.2025 (የተሻሻለ: 14:04 31.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቡናን ለምግብና መጠጥ ቱሪዝም ልማት ለመጠቀም እየሠራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ
የቡናን ታሪክና እሴት ከባሕላዊ ቱሪዝም ጋር በማቀናጀት የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ገጽታ ለመገንባትና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን በመሳብ ዘርፉን ለመጠቀም ማለሙን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የቡናን ባሕል በተግባር የሚመለከቱበትን ዕድል በማመቻቸት የቱሪዝም ዘርፉን አማራጮች ለማስፋት በቅንጅት እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ጎብኚዎች ከቡና ሥነ-ሥርዓት ባለፈ የቡና ለቀማና የደን ምርት አሰባሰብ ሂደት ላይ እንዲሳተፉ እንደሚደረግም ተጠቁሟል።
የቡና ምርት በሰፊ የሚገኝባቸው እንደ ይርጋለም፣ ይርጋጨፌ፣ ጅማ እና ከፋ ያሉ አካባቢዎች ለዚህ የቱሪዝም ዘርፍ በዋነኛነት ተለይተዋል ሲል የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X