በአማራ ክልል የሚገኙ 15 ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ሥርዓቶች የሕጋዊነት ዕውቅና ተሰጣቸው
12:03 31.12.2025 (የተሻሻለ: 12:04 31.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአማራ ክልል የሚገኙ 15 ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ሥርዓቶች የሕጋዊነት ዕውቅና ተሰጣቸው
በክልሉ ምክር ቤት ፀድቀው እውቅና ያገኙት የግጭት መፍቻ ሥርዓቶች፤ የሀገር ሽማግሌዎች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች ሕጋዊ ተቀባይነትና አስገዳጅነት እንዲኖራቸው ያስችላል ሲሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው ተናግረዋል።
የግጭት መፍቻ ሂደቶቹ የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጡ በመሆናቸው ተጠሪነታቸው ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
እውቅና ያገኙት ባሕላዊ ፍርድ ቤቶች፦
ሽምግልና፣ አበጋር፣ ረከቦት፣ ዱለት፣ አማሬ ቁና፣ አውሳይድ፣
ጎራው አባ አሊ፣ ስምንቱ ማይ ቤት፣ ዘወልድ፣ መዛርድ፣
ክፍሎ፣ ሰንዬሰገድ፣ አባ ሀጋ፣ ዙፋን ዋልዋጅ እና ሰባቱ ከዘራ ናቸው።
አስቀድሞ በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚታወቁት እና አሁን ላይ ሕጋዊ ዕውቅና የተሰጣቸው የግጭት መፍቻ ሥርዓቶች በክልሉ በሚገኙ ከ4 ሺህ በላይ ቀበሌዎች ላይ በስፋት ተግባራዊ እንደሚደረጉም ተጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X