የሳኅል ሀገራት ጥምረት እጀ ዙር ቅኝ አገዛዝ ዛቻዎች እና የፈረንሳይን የሲ.ኤፍ.ኤ ፍራንክ ወጥመድ በመቋቋም በ2025 በጥንካሬው ቀጥሏል - ኒጀራዊ ተንታኝ

የሳኅል ሀገራት ጥምረት እጀ ዙር ቅኝ አገዛዝ ዛቻዎች እና የፈረንሳይን የሲ.ኤፍ.ኤ ፍራንክ ወጥመድ በመቋቋም በ2025 በጥንካሬው ቀጥሏል - ኒጀራዊ ተንታኝ
የሳህል ሀገራት ጥምረት በቅርቡ ያካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ድርጅቱ "እየጠነከረ" መምጣቱን እንደሚያሳይ እና በዚህ ዓመት በርካታ ተቋማት መቋቋማቸውን ኢሱፉ ቡባካር ካዶ ማጋጊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ሆኖም መሻሻሎች ቢኖሩም ጥምረቱ አሁንም ተግዳሮቶች ተደቅነውበታል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል፡፡
ደህንነት፦
ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር "በሽብርተኞች፣ በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች እና በታጠቁ ሽፍቶች አማካኝነት በዋናዎቹ አዲስ የቅኝ አገዛዞች እና ተስፋፊ የዓለም ኃይሎች የሚደራጁትን ወታደራዊ ጥቃት "ለመመከት ወደ አዲስ ስትራቴጂካዊ አጋሮች በተለይም ወደ ብሪክስ ለመዞር ተገደዋል።
ባለሙያው አሜሪካ በናይጄሪያ ሶኮቶ ክልል በፈጸመችው የአየር ድብደባ ዙሪያ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ይህ ተግባር "አሜሪካ በኒጀር ድንበር ጦሯን እንድታሰፍር ስለሚረዳት" የሳኅል ሀገራትን ሰላም ለማናጋት የታቀደ "የጮሌ ሴራ" ነው ብሎ እንደሚያምኑ ጠቁመዋል።
ኢኮኖሚ፦
"የሉዓላዊነት ጥያቄው ይህ ነው፦ ከፈረንሳይ የሲ.ኤፍ.ኤ ፍራንክ አስተዳደር ጋር ተሳስረን እንዴት ሉዓላዊ መሆን እንችላለን?"
"ውጤታማ ለመሆን የሳኅል ጥምረት አባል ሀገራት በተቻለ ፍጥነት የራሳቸውን ገንዘብ መፍጠር ይኖርባቸዋል።"
"የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ዋጋ ያስከፍላል፤ ይህ ዋጋ ደግሞ ለኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እድገት ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ መከፈል አለበት።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X