ሁኔታዎች በጥንቃቄ ካልተያዙ የሶማሌላንድ እውቅና ቀጣናውን ማተራመሱ አይቀሬ ነው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሁኔታዎች በጥንቃቄ ካልተያዙ የሶማሌላንድ እውቅና ቀጣናውን ማተራመሱ አይቀሬ ነው - ባለሙያ
ሁኔታዎች በጥንቃቄ ካልተያዙ የሶማሌላንድ እውቅና ቀጣናውን ማተራመሱ አይቀሬ ነው - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.12.2025
ሰብስክራይብ

ሁኔታዎች በጥንቃቄ ካልተያዙ  የሶማሌላንድ እውቅና ቀጣናውን ማተራመሱ አይቀሬ ነው - ባለሙያ

የሶማሌላንድ እውቅና በአካባቢው የሚገኙ እንደ ፑንትላንድ ያሉ ራስ ገዝ አስተዳደሮች እርምጃውን እንዲከተሉ መነሳሳት ሊፈጠር ይችላል፤ ሲሉ ዓለምአቀፍ የሕግ ባለሙያ አንዷለም በእወቀቱ ለስፑቲኒክ አፍሪካ ተናገሩ፡፡

“አሁን በጥንቃቄ ካልተያዘ [...] ምስራቅ አፍሪካ ላይ በቅርብ ደቡብ ሱዳን ተወለደች፣ ከደቡብ ሱዳን ጥቂት ዓመታት በፊት ኤርትራ ተወለደች፤ ... ከዚያ ፑንትላንድ እያለ ይቀጥላል። [...] ተከታታይ ክስተቶች እያየን እንገኛለን፤ እነዚህ ክስተቶች በክልላዊ እይታ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸው በመሆኑ፣ ቀድሞውኑ ያልተረጋጋውን ቀጣና ወደ ከረረ ግጭት ውስጥ ይገፋሉ ብዬ አምናለሁ፡፡" ሲሉ ምልከታቸውን አስረድተዋል።

አንዷለም እስራኤል ለሱማሊላንድ የሰጠችው የአገርነት እውቅና ሆን ብላ አካባቢውን ለማተራመስ ላይሆን እንደሚችል ገልጸው ይዞት የሚመጣው መዘዝ መኖሩን ግን ጠቁመዋል፡፡

" የእስራኤል በቀጣናው መገኘት ችግሮችን መፍጠሩ አይቀሬ ነው። [...] ሆን ብላ ነው ወይስ የሚለውን ጉዳይ ለመፍታት ወደፊት የተወሰኑ ሁኔታዎችን ማየት ይኖርብናል" ሲሉ በቀጣናው የተለያዩ አጀንዳ ያላቸው ሀገራት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0