ሳዑዲ ዓረቢያ በምስራቅ የመን ያካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ሳዑዲ ዓረቢያ በምስራቅ የመን ያካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን አስታወቀች

​በሳውዲ የሚመራው የአረብ ጥምረት፣ ለደቡባዊ የሽግግር ምክር ቤት ኃይሎች የታሰበ ወታደራዊ ጭነት ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ፣ በምስራቅ የመን በሚገኘው አል ሙከላ ወደብ ላይ ያካሂደው የነበረውን ወታደራዊ ዘመቻ ማብቃቱን የኤስፒኤ የዜና ወኪል ዘግቧል።

​የዜና ወኪሉ በሳውዲ የሚመራውን ጥምረት ጠቅሶ እንደዘገበው፣ “በአል ሙከላ ወደብ የተደረገው ውስን ወታደራዊ ዘመቻ ተጠናቅቋል፤  የወደብ እንቅስቃሴዎችም ወደ መደበኛ ተግባራቸው ተመልሰዋል።”

​በመግለጫው እንደተገለጸው፣ በዘመቻው ምክንያት ምንም ዓይነት የሰው ሕይወት መጥፋት ወይም ተጨማሪ ጉዳት አልደረሰም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0