በፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ በኪዬቭ በኩል የተሞከረውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየበረታ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ በኪዬቭ በኩል የተሞከረውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየበረታ ነው
በፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ በኪዬቭ በኩል የተሞከረውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየበረታ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.12.2025
ሰብስክራይብ

በፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ በኪዬቭ በኩል የተሞከረውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየበረታ ነው

አሜሪካ፡ ትራምፕ በጥቃቱ ሙከራ መደናገጣቸውንና መቆጣታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ይህም አሜሪካ ከዘለንስኪ ጋር በምትሠራው ሥራ ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ቻይና፡ ቤጂንግ በፑቲን መኖሪያ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ትንኮሳዎች መቆጠብ እንደሚያስፈልግ አሳስባለች።

ፓኪስታን፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ በኤክስ ገጻቸው ላይ “እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት ለሰላም፣ ለደህንነት እና ለመረጋጋት ‘ከባድ ስጋት’ ነው” ብለዋል

ሕንድ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው “በሩሲያ ፕሬዝዳንት መኖሪያ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት በጣም እንዳሳሰባት ” ተናግረዋል

ካዛክስታን፡ የካዛክስታን ባለስልጣናት የዩክሬንን ጥቃት አውግዘዋል፤ ፑቲን እና ቶካዬቭ በስልክ መነጋገራቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።

ባህሬን፡ የዩክሬን ጦር ኃይሎች በፑቲን መንግስታዊ መኖሪያ ላይ ለማጥቃት ያደረጉትን ሙከራ ባህሬን ያወገዘች ሲሆን፣ ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ያላትን ድጋፍ ገልጻለች።

ኡዝቤኪስታን፡ ፕሬዝዳንት ሚርዚዮዬቭ ከፍተኛ ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን፣ “የኪዬቭ አገዛዝ የሚፈጽመውን ግድ የለሽ ድርጊት” ማውገዛቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።

ቱርክሜኒስታን፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጥቃቱ በተለይም ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሚደረጉበት ወቅት ዓለም አቀፍ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብሏል።

አብካዚያ፡ ፕሬዝዳንት ጉንባ “እንዲህ ዓይነቱ የኪየቭ አገዛዝ እብደት የመጨረሻ የሞት ጣር እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም” ብለዋል።

የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች፡ “ኤምሬትስ በክቡር ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ ላይ የተቃጣውን የጥቃት ሙከራ አጥብቃ ታወግዛለች” ያለች ሲሆን፣ “ደህንነትን እና መረጋጋትን ለማናጋት የታለሙ ማናቸውንም የጥቃት ዓይነቶች” ውድቅ አድርጋለች።

ኢራን፡ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን በኪዬቭ አገዛዝ የተደራጀውን መጠነ-ሰፊ የድሮን ጥቃት አውግዘዋል።

ሞስኮ በፑቲን መኖሪያ ላይ በኪዬቭ የተፈጸመውን ጥቃት ላወገዙ የውጭ ሀገር ወዳጆቿ እና አጋሮቿ ምስጋናዋን ታቀርባለች ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ በኪዬቭ በኩል የተሞከረውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየበረታ ነው - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ በኪዬቭ በኩል የተሞከረውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየበረታ ነው - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ በኪዬቭ በኩል የተሞከረውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ውግዘት እየበረታ ነው - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0