እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷ የእስራኤል እና ሃውቲ ግጭት በአፍሪካ ቀንድ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱእስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷ የእስራኤል እና ሃውቲ ግጭት በአፍሪካ ቀንድ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል - ባለሙያ
እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷ የእስራኤል እና ሃውቲ ግጭት በአፍሪካ ቀንድ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.12.2025
ሰብስክራይብ

እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷ የእስራኤል እና ሃውቲ ግጭት በአፍሪካ ቀንድ እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል - ባለሙያ

የእስራኤል ውሳኔ የራሷን ጥቅሞች ማዕከል ያደረገ እና የቀጣናውን ሰላም የሚያናጋ መሆኑን ጠበቃና የሕግ አማካሪው አንዷለም በእወቀቱ ለስፑቲኒክ አፍሪካ ተንናግረዋል፡፡ ከሁቴ ታጣቂ ጋር የመፋለሚያ ዐውድ ማግኘት አንደኛው ጥቅም ነው ብለዋል፡፡  

" ... የሃውቲ አማጽያን ወደ እስራኤል አንዳንድ ጥቃቶችን የሰነዘሩ ነው፤ አካባቢውን በሚያተራመስ መልኩ እየተቆጣጠሩት ነው። ... አሁን እተሰጠ ያለው ግምት እስራኤል የባሕር የጦር ሰፈር ቀጥታ ይኖራታል ነው። ስለዚህ ከባሕር ላይ ብቻ ሳይሆን ከመሬት ላይም የጦር ሰፈር ገንብተህ ከሶማሊላንድ ወደ ሀውቲዎች ጋር መታኮስ ቀላል ነው"  ሲሉ የእስራኤልን አምጣጥ ገምተዋል፡፡

በሌላ በኩል የእስራኤልን እንቅስቃሴ በመካከለኛው ምስራቅ ካለው የፍልስጤም እና የእስራኤል ገጭት ጋር በቀጥታ ያገናኙታል፡፡

" ... በምላሹ የጋዛ ተፈናቃዮችን ሶማሊላንድ ለማስፈር እስራኤል ብትጠይቅ ሶማሊላንድ በቀላሉ እሺ ትላለች ተብሎ ይታሰባል። ምክንያቱም በብዙ አቅጣጫ ስታየው ሶማሊላንድ አሁን ያገኘችው እውቅና ከየትም የማይገኝ ስጦታ ነው " ሲሉ አሰተያየታችወን ሰጥተዋለ፡፡



አንዷልም እንዳብራሩት፣ በቀጣናው ፍላጎት ያላቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ሲጨመሩ አካባቢው “የለየለት ትርምስ ውስጥ መግባትቱ አይቀርም።”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0