ፕሬዝዳንት ፑቲን ለአፍሪካ መሪዎች፣ ለደቡባዊ ዓለም መሪዎች እና ለዓለም ታዋቂ ሰዎች የአዲስ ዓመት መልካም ምኞቶችን ላኩ

ፕሬዝዳንት ፑቲን ለአፍሪካ መሪዎች፣ ለደቡባዊ ዓለም መሪዎች እና ለዓለም ታዋቂ ሰዎች የአዲስ ዓመት መልካም ምኞቶችን ላኩ
የሩሲያው ፕሬዝዳንቱ አኅጉሪቱ ላይ የቀጠለውን የሞስኮ ተሳትፎ ለማጉላት ለብዙ የአፍሪካ መሪዎች የአዲስ ዓመት መልካም ምኞቶችን ልከዋል ሲል ክሬሚሊን አስታውቋል።
መልዕክቱ ከደረሳቸው የአፍሪካ መሪዎች መካከል የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ይገኙበታል።
ፑቲን በተጨማሪም ለብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፣ ለኩባው መሪ ሚጌል ዲያዝ-ካኔል ቤርሙዴዝ፣ ለቬኔዝዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ለኒካራጓ ተባባሪ ፕሬዝዳንቶች ዳንኤል ኦርቴጋ እና ሮዛሪዮ ሙሪሎ ጨምሮ በመላው ደቡባዊ ዓለም እና ላቲን አሜሪካ ለሚገኙ መሪዎች የበዓል መልዕክቶችን ልከዋል።
መልካም ምኞት የደረሳቸው ሌሎች የሀገር መሪዎች የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የቻይናው መሪ ሺ ጂንፒንግ፣ የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ፣ የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን እና የሰርቢያ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ቩቺች ይገኙበታል።
ከአውሮፓ መሪዎች መካከል ደግሞ ለሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን እና ለስሎቫክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ የመልካም ምኞት መግለጫው ተልኳል።
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ አሥራ አራተኛም ተልኳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X