ሶማሊያ ግዛቷ ለአስገዳጅ የህዝብ ዝውውርም ሆነ ለውጭ ሀገራት የጦር ሰፈርነት እንዲውል እንደማትፈቅድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሶማሊያ ግዛቷ ለአስገዳጅ የህዝብ ዝውውርም ሆነ ለውጭ ሀገራት የጦር ሰፈርነት እንዲውል እንደማትፈቅድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
ሶማሊያ ግዛቷ ለአስገዳጅ የህዝብ ዝውውርም ሆነ ለውጭ ሀገራት የጦር ሰፈርነት እንዲውል እንደማትፈቅድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.12.2025
ሰብስክራይብ

ሶማሊያ ግዛቷ ለአስገዳጅ የህዝብ ዝውውርም ሆነ ለውጭ ሀገራት የጦር ሰፈርነት እንዲውል እንደማትፈቅድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ መሐመድ ዑመር፣ እስራኤል ለሶማሊላንድ እንደ ገለልተኛ አካል የሰጠችውን "ህገ-ወጥ" እውቅና ሀገራቸው በጥብቅ እንደምትቃወም ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው በሞቃዲሾ ለሚገኙ የዓለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በሰጡት መግለጫ፣ "የሶማሊያ ፌደራላዊ መንግስት ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ ውድቅ ያደርጋል ... ማንኛውም የውጭ አካል የሶማሊያን የግዛት ሁኔታ የመቀየር ህጋዊ ስልጣን የለውም" ብለዋል።



ሶማሊላንድ የሶማሊያ ሉዓላዊ ግዛት የማይነጠል አካል መሆኑን፣ ይህም በሶማሊያ የሽግግር ሕገ-መንግሥት፣ በተመድ ቻርተር እና በአፍሪካ ሕብረት መስራች ሰነድ የተጠበቀ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

እንዲህ ዓይነቱ እውቅና ዓለም አቀፍ ህግን የሚጻረር፣ የሶማሊያን መንግስት የመገንባት ጥረት የሚያደናቅፍ እና ለአክራሪ ቡድኖች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢ አለመረጋጋት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑን ኡመር አስጠንቅቀዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ማጠቃለያ ላይ ሶማሊያ ለፍልስጤማውያን መብት ያላትን ድጋፍ በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ሀገራቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘውን ድንበሯን ለመከላከል ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ እርምጃዎችን እንደምትወስድ አስታውቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0