ሩዋንዳ እና ደቡብ አፍሪካ ለሶማሊያ የግዛት አንድነት ያላቸውን ድጋፍ ዳግም አረጋገጡ
15:00 30.12.2025 (የተሻሻለ: 15:04 30.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩዋንዳ እና ደቡብ አፍሪካ ለሶማሊያ የግዛት አንድነት ያላቸውን ድጋፍ ዳግም አረጋገጡ
ሩዋንዳ ከአፍሪካ ሕብረት እና ከምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጎን በመሰለፍ ለሶማሊያ ያላትን ድጋፍ የገለጸች ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት በጋራ ሰላም እና ብልጽግና ላይ የተመሰረተ የቀጣይ ጉዞ እንዲኖር ማበረታቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ እስራኤል ለሶማሊላንድን እንደ ነፃ ሀገር እውቅና መስጠቷን በተመለከተ ያላትን ስጋት ገልጻለች። ይህ ድርጊት የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚጥስ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሰላም አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አስታውቃለች።
ደቡብ አፍሪካ "አንድ ሀገር ነፃነቷን ስታገኝ የነበራትን ድንበር ይዛ ትቀጥላለች የሚለውን" የአፍሪካ ሕብረት መርህ በድጋሚ በማረጋገጥ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ውድቅ እንዲያደርግ እና አንዲት የጸናች እና የተረጋጋች ሶማሊያን እንዲደግፍ አሳስባለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/