ሩሲያ፣ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና ለሶማሊያ ሉዓላዊነት ስጋት ነው ስትል በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አወገዘች
14:16 30.12.2025 (የተሻሻለ: 14:24 30.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ፣ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና ለሶማሊያ ሉዓላዊነት ስጋት ነው ስትል በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አወገዘች
ሩሲያ፣ እስራኤል ታኅሣሥ 17 ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና የሶማሊያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት የሚሸረሽር ፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያለው እርምጃ ነው ስትል በተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ “ጥልቅ ስጋቷን” ገልጻለች።
የሩሲያ የተመድ ተወካይ ዲና ጊልሙትዲኖቫ ይህ ውሳኔ በሶማሊያ፣ በአፍሪካ ሕብረት፣ በአረብ ሊግ እና በክልላዊ መንግሥታት ጠንካራ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን በመጥቀስ፣ በቀታናው እና ባሻገር ውጥረት የማባባስ አደጋ እንዳለው አስጠንቅቀዋል።
“አፍሪካ አሁንም ድረስ... በፀረ-ቅኝ ግዛት ጎራ ንቁ ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ትሻለች። እውነተኛ፣ ነጻ እና ስኬታማ የአፍሪካ የዕድገት ሞዴሎችን መገንባት የሚደግፉ ምክንያታዊ አገራት በሙሉ እነዚህን ጥረቶች እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን።”
እስራኤል እ.ኤ.አ. በ1991 እራሷን ነጻ አገር ብላ ካወጀች በኋላም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላገኘችውን ሶማሊላንድን በይፋ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። በሞቃዲሾ የሚገኘው የሶማሊያ መንግሥት ይህንን እርምጃ “በሉዓላዊነት ላይ የተደረገ ወረራ” ሲል አውግዞታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X