ኢትዮ ቴሌኮም በማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች፣ የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች መጨመር ምክንያት የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ አስታወቀ
18:32 29.12.2025 (የተሻሻለ: 18:34 29.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮ ቴሌኮም በማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች፣ የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች መጨመር ምክንያት የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ አስታወቀ
ድርጅቱ የዋጋ "ማስተካከያውን" ያደረገው፣ የሚሰጠውን ሰፊ አገልግሎት ቀጣይነት ለማረጋገጥ እና በመላ ሀገሪቱ እያካሄደ ያለውን የቴሌኮሙኒኬሽን እና ዲጂታል መሠረት ልማት ለማስፋፋት መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ማስተካከያው አካታችነት እና የደንበኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ በርካታ ደንበኞች የሚገለገሉባቸውን አነስተኛ ጥቅሎች እና የአካል ጉዳተኞች፣ የተማሪዎች እና የመምህራን ጥቅሎች የዋጋ ጭማሪ አልተደረገባቸውም ብሏል።
ከ85 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እና ከ56 ሚሊዮን በላይ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን ማፍራቱን ኩባንያው ጨምሮ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X