የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታካሚ ሕጻናት ድጋፍ አደረገ
17:30 29.12.2025 (የተሻሻለ: 17:44 29.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኤምባሲ ለካንሰር ታካሚ ሕጻናት ድጋፍ አደረገ
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ከሩሲያ የሳይንስ እና የባሕል ማዕከል ጋር በመተባበር በተስፋ አዲስ ፓረንት ቻይልድሁድ ካንሰር ድርጅት ውስጥ ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ የካንሰር ታማሚ ሕጻናት የጎርጎሮሳውያኑን አዲስ ዓመት አስመልክቶ የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭጌኒ ተረኺን ለሕጻናቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን በድርጅቱ ለሚገኙ ሕጻናት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የተስፋ አዲስ ፓረንት ቻይልድሁድ ካንሰር ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሳራ ኢብራሂም ለስፑትኒክ ኢትዮጵያ እንደገለጹት የሩሲያ ኤምባሲ በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙት ሕጻናት በዓመት ከሦስት እስከ አራት ጊዜ የመድኃኒት፣ የምግብ ግብዓቶች እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማደረግ ላይ ይገኛል።
ኤምባሲው እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ ሕጻናቱ ተገቢውን ሕክምና አግኝተው ጤናማ ተተኪ ሕጻናት እንዲሆኑ እያደረገው ላለው ጥረት ውጤታማነት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ሥራ አስኪያጇ መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ 

