ትራምፕ የታቀደው የዩክሬን ስምምነት “ለሁሉም መልካም ነው” ብለው ያምናሉ

ሰብስክራይብ

ትራምፕ የታቀደው የዩክሬን ስምምነት “ለሁሉም መልካም ነው” ብለው ያምናሉ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍሎሪዳ በሚገኘው የማር-አ-ላጎ መኖሪያ ቤታቸው ከቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የዩክሬን የሰላም ስምምነት ዕውን እየሆነ እና ሁሉንም ወገን ሊጠቅም የሚችል ነው ብለዋል።

ትራምፕ የሰጧቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦

ትራምፕ፣ ሁለቱም ማለትም የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ዘለንስኪ ሰላም ላይ ለመድረስ የምር ይፈልጋሉ ብለዋል።

መጪው ስምምነት "ለዩክሬን ጥሩ" የሆነ እና "ለሁሉም መልካም" እንደሚሆን ያምናሉ፡፡

ትራምፕ ድርድርን ለመቀጠል ከዘለንስኪ ጋር ከተገናኙ በኋላ ፑቲን ጋር ደግመው እንደሚደውሉ ገልጸዋል፡፡

ንግግሮቹ ውስብስብ ቢሆኑም "ያን ያህል ውስብስብ አይደሉም" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ስምምነቱ የአውሮፓ አገራት ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያደርጉበት የደህንነት ዝግጅቶችን እንደሚያካትት ትራምፕ ተናግረዋል።

እልባቱ ለዩክሬን ከቀጣይ መጠነ–ሰፊ የመልሶ ግንባታ ሥራ ጋር ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደሚያስገኝም አክለዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0