የፑቲን እና ትራምፕ አንድ ሰዓት ከሩብ የፈጀ የስልክ ውይይት አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፑቲን እና ትራምፕ አንድ ሰዓት ከሩብ የፈጀ የስልክ ውይይት አደረጉ
የፑቲን እና ትራምፕ አንድ ሰዓት ከሩብ የፈጀ የስልክ ውይይት አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.12.2025
ሰብስክራይብ

የፑቲን እና ትራምፕ አንድ ሰዓት ከሩብ የፈጀ የስልክ ውይይት አደረጉ

በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል የተደረገው የስልክ ውይይት የተካሄደው በአሜሪካ በኩል ባለው አነሳሽነት ሲሆን ትራምፕ ከቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት መሆኑን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ተናግረዋል።

በስልክ ውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

የስልክ ውይይቱ የተካሄደው በአሜሪካው ፕሬዝዳንት አነሳሽነት ነው።

ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት በርካታ ጉዳዮችን ለመወያየት ፈልገው ነበር።

የውይይቱ አካሄድ የወዳጅነት፣ ገንቢና ተግባር ተኮር ተብሎ ተገልጿል።

ትራምፕ ግጭቱ በተቻለ ፍጥነት እንዲያልቅ ያለውን ሀሳብ አጥብቀው አቅርበዋል።

ትራምፕ ሩሲያ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ መፍትሄ እንደምትፈልግ እርግጠኛ እንደሆኑ ተናግረዋል።

ዩክሬን መሬት ላይ ያለውን እውነታ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት የዶንባስን ክልል ስለመስጠት በፍጥነት መወሰን አለባት።

ፑቲን እና ትራምፕ በግዛት ስምምነት ላይ ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ በሚል ሰበብ የሚደረግ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ግጭቱን እንደሚያራዝመው ተስማምተዋል።

የግጭቱ የመጨረሻ ፍጻሜ የኪዬቭ አገዛዝ በዶንባስ ላይ በሚወሰነው ውሳኔ ይመሠረታል።

ትራምፕ አሜሪካ ከሩሲያ እና ከዩክሬን ጋር የኢኮኖሚ ትብብር የሚታደርግበትን ተስፋ አጭረዋል።

ፑቲን በሁለት ልዩ የስራ ቡድኖች አማካኝነት የሰላም ጥረቶችን ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ሁለቱ መሪዎች የገና እና የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ተለዋውጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0