በኮት ዲቯር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ዝቅተኛ የመራጮች ተሳትፎ ተመዘገበ
19:40 28.12.2025 (የተሻሻለ: 19:44 28.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኮት ዲቯር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ዝቅተኛ የመራጮች ተሳትፎ ተመዘገበ
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው ምርጫ በ205 የምርጫ ክልሎች 255 የፓርላማ አባላትን ለመምረጥ ከስምንት ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።
ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ሌሊቱን ይፋ ባደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት መሠረት፣ የመራጮች ተሳትፎ 32.34 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህም እ.ኤ.አ. በ2021 ከተካሄደው ያለፈው የፓርላማ ምርጫ ተሳትፎ 37.88 በመቶ ጋር ሲነጻጸር የተወሰነ ቅናሽ አሳይቷል።
255 መቀመጫዎች ያሉት የሀገሪቱ ብሔራዊ ምክር ቤት በአሁኑ ወቅት፣ 163 መቀመጫዎች በፕሬዝዳንት አላሳን ኦዋታራ በሚመራው የሁፉዌቲስቶች ስብስብ ለዲሞክራሲና ለሰላም (RHDP)፣ 66 መቀመጫዎች በኮት ዲቯር ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (PDCI) ፣ 18 መቀመጫዎች የአፍሪካ ሕዝቦች ፓርቲ–ኮት ዲቯር (PPA-CI)፣ እንዲሁም 4 መቀመጫዎች በግል ተወዳዳሪዎች የተያዙ ሲሆን አራት መቀመጫዎች ደግሞ ክፍት ናቸው። ለዘንድሮው ምርጫ ከተመዘገቡት 1,370 ዕጩዎች መካከል 181 ያህሉ ሴቶች ናቸው።
በኮት ዲቯር የነበረውን የምርጫ ድባብ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ በምስል አስቀርቶታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X