🪖 ለዩክሬን የሚሰጠው የደህንነት ዋስትና አሜሪካን ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት ጎትቶ ሊያስገባት ይችላል - ዘገባ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ🪖 ለዩክሬን የሚሰጠው የደህንነት ዋስትና አሜሪካን ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት ጎትቶ ሊያስገባት ይችላል - ዘገባ
🪖 ለዩክሬን የሚሰጠው የደህንነት ዋስትና አሜሪካን ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት ጎትቶ ሊያስገባት ይችላል - ዘገባ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.12.2025
ሰብስክራይብ

🪖  ለዩክሬን የሚሰጠው የደህንነት ዋስትና አሜሪካን ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት ጎትቶ ሊያስገባት ይችላል - ዘገባ

​ዋይት ኃውስ ለዩክሬን “የኔቶን አንቀጽ 5ን” የመሰለ የደህንነት ዋስትና ለመስጠት ያቀረበው ሐሳብ፣ ለዩክሬንና ለአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓና ከዚያም ባሻገር ላሉ የአሜሪካ አጋሮችም ጭምር “ትኩረት ያልተሰጣቸውና ከፍተኛ የሆኑ አደጋዎችን ይዞ ይመጣል” ሲል ዘ ዋሽንግተን ፖስት  ዘግቧል።

​ጋዜጣው፣ አሜሪካ ባቀረበችው ሐሳብ ላይ በርካታ “ከባድ ፈተናዎች” እንዳሉ ያስጠነቀቀ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል “ውስብስብ የሆነው የታማኝነት ጥያቄ” ይገኝበታል።

ዘገባው አክሎም “የአሜሪካን ጦር በዩክሬን ምድር ማሰማራት የአሜሪካንን ወሳኝ ጥቅሞች ለማስጠበቅ አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ ወታደሮቿ ከዓመታት በፊት እዚያ ይገኙ ነበር” ብሏል።

አሜሪካ ለዩክሬን የአንቀጽ 5 ዓይነት የደህንነት ዋስትና ከመስጠት መቆጠብ ያለባትበት ዋነኛው ምክንያት “ይህ ግዴታ ምን ማለት እንደሆነ ከሚያሳየው መሠረታዊ እውነታ የተነሳ ነው፤ ይህም ስለ ዩክሬን ተብሎ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ መሆንን ያመለክታል” ሲል ጋዜጣው አመልክቷል።

​እንዲህ ዓይነቱ ቃል ኪዳን ተግባራዊ ሳይሆን ቢቀር፣ አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ግንባር በመላክ የገባችውን ቃል እንድትፈጽም “ከፍተኛ የፖለቲካ ጫና ይደርስባታል። በዚያን ጊዜ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ ትገባለች፤ ይህም የኒውክሌር ጦርነትን ሊያስከትል የሚችል ውጤት ይኖረዋል” ሲል ጋዜጣዉ ዘገባውን አጠቃልሏል።

የልዩ ዘመቻውን ዳራ ለመረዳት ስፑትኒክ አፍሪካ ያዘጋጀውን ትንታኔ ያንብቡ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0