በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ በድምቀት የተከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል* በፎቶ
16:55 28.12.2025 (የተሻሻለ: 19:34 28.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ በድምቀት የተከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል* በፎቶ
በዓሉ በአገር ውስጥ እንዲሁም ከአገር ውጭ በሚገኙ በርካታ ገዳማት እና አድባራት በቅዳሴ፣ በወረብ፣ በዝማሬ፣ በፀሎትና በሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ–ስርዓቶች ተክበሮ ውሏል፡፡
የንግሥ በዓሉ በጅቡቲ ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሲከበር የቀድሞ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እና የአሁን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ዶ/ር ለገሠ ቱሉ ተገኝተዋል ሲል የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
*በዓሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ዳን. 3፥1-30 በሚገኘው ታሪክ መሠረት ቅዱስ ገብርኤል አዛርያ፣ አናንያ እና ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕፃናትን ከንጉሥ ናቡከደነፆር የእቶን እሳት ያዳነበት ቀን መታሰቢያ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X






