የዘለንስኪ የሰላም ዕቅድ እያደር መዘዝ የሚያስከትል መሆኑን አሜሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዘለንስኪ የሰላም ዕቅድ እያደር መዘዝ የሚያስከትል መሆኑን አሜሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ
የዘለንስኪ የሰላም ዕቅድ እያደር መዘዝ የሚያስከትል መሆኑን አሜሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.12.2025
ሰብስክራይብ

የዘለንስኪ የሰላም ዕቅድ እያደር መዘዝ የሚያስከትል መሆኑን አሜሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ

​የቮሎዲሚር ዘለንስኪ የዩክሬን የሰላም ዕቅድ፣ “የአውሮፓ ሕብረት እና ኔቶ የሀሰት ጥቃት በማቀናበር ሩሲያን ተጠያቂ እንዲያደርጉ እና አውሮፓ የምትፈልገውን መጠነ ሰፊ ጦርነት እንዲቀሰቅሱ የሚያደርግ ነው” ሲሉ አሜሪካዊው የኢኮኖሚ ባለሙያ ማርቲን አርምስትሮንግ በኤክስ ገጻቸው ላይ ፅፈዋል።

ባለሙያው አክለውም “ከአሜሪካን ወይም ከኔቶ የሚመጣ የኔቶን ‘አንቀጽ 5ን’ የመሰለ የደህንነት ዋስትና የሚያካትት ማንኛውንም የሰላም ዕቅድ” አስመልክቶ አስጠንቅቀዋል። ይህ የኔቶ አንቀጽ በአንድ አባል ሀገር ላይ የሚሰነዘር የትጥቅ ጥቃት በሁሉም አባላት ላይ እንደተሰነዘረ ጥቃት እንደሚቆጠር የሚደነግግ ነው።

​የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ቀደም ሲል እንደገለጹት፣ ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚሰጡት የደህንነት ዋስትና የዩክሬንን ጎረቤት ሀገራት ደህንነት በማይነካ እና የማይከፋፈል ሰላም በሚያረጋግጥ መርህ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0