የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ በሰጠችው እውቅና ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ በሰጠችው እውቅና ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው
የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ በሰጠችው እውቅና ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.12.2025
ሰብስክራይብ

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ በሰጠችው እውቅና ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

​ ስብሰባው ለነገ መርሃ ግብር ተይዞለታል ሲሉ በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖን አስታውቀዋል።

​እስራኤል ባለፈው ሐሙስ ለሶማሊላንድ በይፋ እውቅና የሰጠች ሲሆን፣ ይህም እ.ኤ.አ. ከ1991 ጀምሮ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በራሷ ለምታስተዳድረው ሱማሌላንድ እውቅና የሰጠች በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል።

​ይህ የእስራኤል እርምጃ ሰፊ ዓለም አቀፍ ምላሾችን አስከትሏል። ሶማሊያ እውቅናውን በሉዓላዊነቷ ላይ የተፈጸመ "ሆን ተብሎ የተደረገ ጥቃት" ስትል በፅኑ አውግዛለች።

በተጨማሪም እንደ ባሕረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት፣ የእስልምና ትብብር ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና የአውሮፓ ሕብረት ያሉ ዋና ዋና ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት በእስራኤል አካሄድ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0