የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ነው
12:15 28.12.2025 (የተሻሻለ: 12:24 28.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ነው
ታኅሣሥ 19 የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በርካታ ገዳማት እና አድባራት የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥነ–ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እና ሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በዓሉ በልዩ ድምቀት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ብቻ መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፣ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ጨምሮ ከ54 በላይ ገዳማትና አድባራት ላይ የንግሥ በዓሉ ይከበራል፡፡
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ 




