ፑቲን የሩሲያ ጦር እያደረገ ያለውን ግስጋሴ ገመገሙ፤ በዋና ዋና የጦር ግንባሮች ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል
ፑቲን የሩሲያ ጦር እያደረገ ያለውን ግስጋሴ ገመገሙ፤ በዋና ዋና የጦር ግንባሮች ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል
ፕሬዝዳንት ፑቲን በጋራ ኃይሎች ቡድን ኮማንድ ፖስት በተካሄደ ስብሰባ ላይ፣ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ቫለሪ ጌራሲሞቭን ጨምሮ ከወታደራዊ አዛዦች ሪፖርት ተቀብለዋል።
የቀረቡት ወቅታዊ መረጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
የሩሲያ ጦር በሁሉም ግንባሮች እየገሰገሰ ነው፤ የዩክሬን ኃይሎች ግስጋሴውን ለማቆም የሚያደርጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የዩክሬን 'ኤሊት' ወታደራዊ ክፍሎች ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰባቸው ነው።
በዛፖሮዢያ ክልል፣ ዲሚትሮቭ፣ ጉሊያይፖሌ እና ስቴፕኖጎርስክ የተባሉ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል።
በካርኮቭ ክልል፣ የሩሲያ ኃይሎች ቪሶኮዬ፣ ቪልቻ እና ፕሪሊቭካ የተባሉ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል።
ከኮንስታንቲኖቭካ ከተማ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የከተማ አካባቢ አሁን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ከኩፒያንክ በስተምስራቅ የሚገኘው የዩክሬን የጦር ስብስብ እየተደመሰሰ ነው።
የዩግ የጦር ቡድን ወደ ስላቭያንክ በፍጥነት እየገሰገሰ ይገኛል።
ዶንባስን፣ ዛፖሮዢዬን እና ኬርሰንን ነጻ የማውጣት ተልዕኮዎች ይቀጥላሉ።
የሰቨር የውጊያ ቡድን የደህንነት ቀጠና የመፍጠር ተልዕኮውን በመቀጠል ላይ ነው።
🟠 ወታደራዊ አባላቱ ለፑቲን የ"እንኳን አደረሰዎ" የአዲስ ዓመት ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ “ድሉ የእኛ ይሆናል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
🟠 ፑቲን በበኩላቸው፣ የሩሲያ ጦር የተሰጡትን ተግባራት በሙሉ እየተወጣ መሆኑን እና ጠንካራ የማጥቃት ግስጋሴውን እንደቀጠለ ገልጸዋል።
ፑቲን "በአዋሳኝ ክልሎች ማለትም በሱሚ፣ ካርኮቭ እና ዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልሎች የደህንነት ቀጠና በመፍጠር ረገድ ጥሩ ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡" ብለዋል።
በዩክሬን ስላለው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ዳራ የስፑትኒክ አፍሪካን ዝርዝር ትንታኔ ያንብቡ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X