በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተሰማሩት የብሩንዲ ወታደሮች ስጋቶች እስኪወገዱ ድረስ በሀገሪቱ ይቆያሉ - ፕሬዝዳንቱ
20:02 27.12.2025 (የተሻሻለ: 20:04 27.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተሰማሩት የብሩንዲ ወታደሮች ስጋቶች እስኪወገዱ ድረስ በሀገሪቱ ይቆያሉ - ፕሬዝዳንቱ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ደህንነት የብሩንዲም ደህንነት ነው፤ የጎረቤት ሀገር ምስራቃዊ ግዛቶችም ለብሩንዲ የመጀመሪያው የመከላከያ ግንባር ናቸው ሲሉ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በዓመታዊ ግምገማቸው ወቅት ተናግረዋል።
የብሩንዲ ኃይሎች በሁለቱም ሀገራት ላይ ስጋት የሆኑ የታጠቁ ቡድኖችን ለመዋጋት ከኮንጎ ጦር ጋር በመቀናጀት ላይ መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥተዋል። በተለይም ደቡብ ኪቩን እንደ መሸሸጊያ በመጠቀም በብሩንዲ ላይ ጥቃት የሚሰነዝረውን የሬድ-ታባራ አማፂ ቡድንን ጠቅሰዋል።
በኪንሻሳ ጥያቄ መሰረት እ.ኤ.አ. ከ2023 ጀምሮ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተሰማራው የብሩንዲ ጦር በዋናነት በደቡብ ኪቩ ግዛት ይገኛል። በቅርቡም ከኤም23 አማፂያን ጋር በተደረገ ውጊያ ላይ ተሳትፎ ጉዳት ደርሶበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X