ኒጀር የሳሕል ጥምረት ባዮሜትሪክ* ብሔራዊ መታወቂያ ካርድን አፀደቀች
19:25 27.12.2025 (የተሻሻለ: 19:34 27.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኒጀር የሳሕል ጥምረት ባዮሜትሪክ* ብሔራዊ መታወቂያ ካርድን አፀደቀች
🪪 ኒጀር ከሳሕል ሀገራት ጥምረት ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ባለብዙ ተግባር ኤሌክትሮኒክ ስማርት ካርድ አስተዋውቃለች።
ይህ እርምጃ የሚከተሉትን ለማድረግ ያለመ ነው፦
በኮንፌዴሬሽኑ ውስጥ የሰዎች ነፃ እንቅስቃሴን ማመቻቸት፣
ቀጣናዊ ውህደትን ማጠናከር፣
ዘመናዊ እና አስተማማኝ የመታወቂያ ሰነድ ማቅረብ።
ካርዱ አሁን ዕድሜያቸው 15 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉም የኒጀር ዜጎች ግዴታ ሆኗል።
ካርዱን የሚያቋቁመው አዋጅ በትናንትናው ዕለት በኒጀር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቋል። የአዋጁ አፈጻጸም ሂደቶችን እና ደንቡን ላለማክበር የሚጣል ቅጣቶችን ይዘረዝራል።
*የጣት ዐሻራ፣ የፊት፣ የዐይን እና ሌሎችም የአካል ክፍል መረጃን የሚይዝ የመታወቂያ ካርድ አይነት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X