ሩሲያ አፍሪካ ውስጥ የአደጋ አስተዳደር ማዕከላትን ለማቋቋም እያጤነች ነው
18:20 27.12.2025 (የተሻሻለ: 18:24 27.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ አፍሪካ ውስጥ የአደጋ አስተዳደር ማዕከላትን ለማቋቋም እያጤነች ነው
ማዕከላቱ ከእሳት አደጋ ተከላካዮች እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የሥልጠና ፕሮግራሞች ጋር በአንድነት በጎርጎሮሳዊያኑ 2026 ሊተገበሩ ይችላሉ ሲል የሩሲያ የአደጋ ጊዜ ሁኔታዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስትሩ አሌክሳንደር ኩሬንኮቭ እነዚህን ዕቅዶች በዛሬው ዕለት በተከበረው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቀን ላይ ይፋ አድርገዋል።
ተነሳሽነቱ በርካታ የዓለም ቀጣናዎችን የሚያካትት ሲሆን አኅጉረ አፍሪካ፣ እስያ-ፓሲፊክ፣ መካከለኛው እስያ እና መካከለኛው ምሥራቅ ይገኙበታል።
ሚኒስትሩ፣ የአደጋ ጊዜ ሁኔታዎችን ለመከላከል፣ መዘዞችን ለማስተዳደር እና ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፣ ተዛማጅነት ያላቸው ፕሮቶኮሎች አስቀድመው የተፈረሙ ሲሆን ከውጭ ኤጀንሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚደረጉት ስምምነቶች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X