የኒጀር መንግሥት አጠቃላይ የክተት አዋጅ ረቂቅን አፀደቀ
16:05 27.12.2025 (የተሻሻለ: 16:14 27.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኒጀር መንግሥት አጠቃላይ የክተት አዋጅ ረቂቅን አፀደቀ
የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የውሳኔ ሃሳቡን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ "አዋጁ ያስፈለገው የሀገሪቱን የግዛት አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ እንዲሁም የህዝቡን፣ የተቋማትን እና የሀገሪቱን ወሳኝ ጥቅሞች ከማንኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ ስጋት ለመጠበቅ ሲባል ነው።" በተጨማሪም "አዋጁ አጠቃላይ የክተት ጥሪን የማደራጀት፣ የማዘጋጀት እና የመፈፀም ሂደቶችን ይገልጻል።"
የአዋጁ ረቂቅ እንደሚጠቅሰው፤ ማንኛውም ዜጋ ከአጠቃላይ የክተት ጥሪ ጋር የተያያዙ ድንጋጌዎችን እና እርምጃዎችን የማክበር ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ ይህም ለውትድርና ጥሪ ፈጣን ምላሽ መስጠትን ይጨምራል።
አዋጁ ለጦር ሠራዊቱ ፍላጎት ሲባል ቁሳቁሶችን እና ተሽከርካሪዎችን በግዳጅ የመውሰድ እድልን ይሰጣል።
አዋጁ ተግባራዊ እንዲሆን በሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ተፈርሞ በኒጀር ሪፐብሊክ ይፋዊ ጋዜጣ ላይ መታተም ይኖርበታል።
🪖 በአሁኑ ወቅት የኒጀር መከላከያ ሠራዊት ቁጥር 40 ሺህ ነው። የሀገሪቱ አመራር ይህንን ቁጥር እ.ኤ.አ. እስከ 2026 ድረስ ወደ 100 ሺህ ለማድረስ አቅዷል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X