የዘለንስኪ የሰላም ዕቅድ ‘ገና ሳይጀመር የከሸፈ ሊሆን ይችላል’ - የቀድሞ የአሜሪካ ጦር መኮንን

ሰብስክራይብ

የዘለንስኪ የሰላም ዕቅድ ‘ገና ሳይጀመር የከሸፈ ሊሆን ይችላል’ -  የቀድሞ የአሜሪካ ጦር መኮንን

​በዘለንስኪ የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ውስጥ "መርዛማ ክኒኖች" (አስቸጋሪ ነጥቦች) እንደሚገኙበትና በተለይም የድንበር ማካለያ መስመርን የሚመለከተው ነጥብ ለሩሲያ "ፈጽሞ የማይታሰብ" መሆኑን የቀድሞ የአሜሪካ ሌተናል ኮሎኔል ዳንኤል ዴቪስ ገለጹ።

ዴቪስ የሩሲያን ሕገ-መንግሥት በመጥቀስ፤ ክሬሚያን እንዲሁም የዶኔትስክ እና የሉጋንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊኮችን ጨምሮ ቀድሞውኑ የሩሲያ አካል በሆኑ ግዛቶች ጉዳይ ላይ "ሞስኮ  ምንም ዓይነት ማመቻመች ውስጥ የምትገባበት መንገድ የለም" ሲሉ አመልክተዋል።

​የቀድሞው የአሜሪካ ጦር መኮንን ሲያብራሩም፣ “ፑቲን በዚህ ጉዳይ ማመቻመች አይችሉም፤ ጥያቄውም በጣም ከባድ ነው። በምዕራባውያንም ሆነ በዩክሬን በኩል ፑቲን እንዲደራደሩ የሚያስገድድ ምንም ዓይነት የመደራደሪያ አቅም የለም። ያለው እውነታ ይሄው ነው” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

​በተጨማሪም የደህንነት ዋስትናን በተመለከተ ሲናገሩ፣ ጉዳዩ “የሩሲያን ደህንነትም ማካተት አለበት እንጂ በሩሲያ ላይ ብቻ የሚደረግ ዋስትና መሆን የለበትም” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0