የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ
የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.12.2025
ሰብስክራይብ

የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ

  በ2025፣ በዓለም አቀፍ የወረርሽኝ ዝግጁነት ቀን፣ ሩሲያ ከአፍሪካ አጋሮች ጋር በመሆን አደገኛ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል፣ ለመለየት እና ምላሽ ለመስጠት ትኩረቱን በአቅም ግንባታ፣ ሳይንስ እና ፈጣን ምላሽ  በማድረግ የሠራቸበትን አጨር ማጠቃለያ እነሆ ቀርቧል፡፡

እየተጠናቀቀው ያለው የጎርጎሮሳውያኑ ዓመት ዋና ዋና ክስተቶች፦

ለወረርሽኝ የተሰጠ ፈጣን ምላሽ

በካምፓላ የኢቦላ በሽታ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ፣ የሩሲያ የሰብአዊ ደህንነት ተቆጣጣሪ፣  ከኡጋንዳ የጤና ባለስልጣናት ጋር በቅርበት በመቀናጀት የምክር አገልግሎት፣ "የኤፒዲሚዮሎጂ" ድጋፍ እና ተንቀሳቃሽ የላብራቶሪ አገልግሎትን በበሽታው በተጠቁ አካባቢዎች አሰማርቷል።

ተንቀሳቃሽ የላብራቶሪዎች በአፍሪካ

🟣 ተንቀሳቃሽ የፀረ- ወረርሽኝ ላብራቶሪዎች ለኮንጎ ሪፐብሊክለማዳጋስካር እና ለቡርኪና ፋሶ ተሰጥተዋል። ላብራቶሪዎቹ በስፍራው ላይ ምርመራ ለማድረግ (ለአንድ ምርመራ እስከ 30 ደቂቃ) እና በቀን ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምርመራዎችን ለማከናወን ያስችላሉ።

🟣 እነዚህ ላብራቶሪዎች የየሀገራቱን የላብራቶሪ መሠረተ ልማት ያጠናከሩ ሲሆን፣ ራቅ ባሉ እና ከፍተኛ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የምርመራ ተደራሽነትን አስፋፍተዋል።

ስልጠና እና የአካባቢ አቅም ግንባታ

🟡 በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ባለሙያዎች በኤፒዲሚዮሎጂ (ወረርሽኝ መከላከል)፣ በላብራቶሪ ምርመራ እና በባዮሎጂካል ደህንነት ላይ ስልጠና ወስደዋል። ይህም በኮንጎ እና በኡጋንዳ የተሰጡ የላቁ ኮርሶችን እና ከአዲሶቹ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎች ጋር የተያያዙ የተግባር ትምህርቶችን ያካትታል።

🟡 እንደ ሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ፣ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ከ200 በላይ አፍሪካውያን ባለሙያዎች በሩሲያ የበሽታ መከላከያ ዘዴዎች ሰልጥነዋል።

‍ መጠነ-ሰፊ የጋራ ልምምዶች እና ምርምር

የመጀመሪያው የሩሲያ-አፍሪካ ዓለም አቀፍ ተላላፊ በሽታዎችን የመከላከል ልምምድ ባለፈው ሚያዚያ ወር በኢትዮጵያ ተካሂዷል። ይህም ከ15 የአፍሪካ ሀገራት፣ ከሩሲያ እና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተውጣጡ ባለሙያዎችን አሳትፏል።

የሮስቦትሬቡዳዞር ኃላፊ አና ፖፖቫ ለስፑትኒክ አፍሪካ ሲናገሩ፣ "እያንዳንዱ ሀገር ስጋቶችን ለይቶ እንዲያውቅ እና ህዝቡን ከአደጋ ለመጠበቅ ትክክለኛ እርምጃዎችን መውሰድ እንዲማር እውቀታችንን፣ ልምዳችንን፣ ቴክኖሎጂዎቻችንን እና ላብራቶሪዎቻችንን እናካፍላለን" ብለዋል።

በሳይንስ መስክ

በማዳጋስካር የሩሲያ እና የሀገር ውስጥ ሳይንቲስቶች የሩሲያ የክትትል ዘዴዎችን እና የተበረከቱ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎችን በመጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጥሮ ወረርሺኝ መገኛዎችን መርምረዋል።

በኡጋንዳ የመጀመሪያው የጋራ ሳይንሳዊ ጉዞ ከ1 ሺህ በላይ የባዮ-ቁስ ናሙናዎችን የሰበሰበ ሲሆን፣ ይህም ስለ ተላላፊ በሽታዎች ያለውን ግንዛቤ አሻሽሏል።

አጋርነትን እና ትስስርን ማስፋፋት

🟠 ከግብፅ፣ ከቡርኪና ፋሶ እና ከሳሕል ሀገራት ጋር ያለው ትብብር ጥልቀት ያለው ሲሆን፣ ለተጨማሪ ስልጠና፣ ለጋራ ምርምር እና ለላብራቶሪ ድጋፍ እቅድ ተይዟል።

🟠 እስከ ባለፈው ታህሳስ 7 ድረስ በሩሲያ የተሰሩ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎች በአፍሪካ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን፣ እስከ 2025 መጨረሻ ድረስ ተጨማሪ አራት ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎች እንደሚቀርቡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በታህሳስ 8 አስታውቋል።

ሊጠናቀቅ አራት ቀናት በቀሩት በጎርጎሮሳውያኑ 2025፣ የሩሲያ የወረርሽኝ ዝግጁነት ጥረትን አስመልክቶ አፍሪካ ውስጥ "ከበላይነት ይልቅ አጋርነትን" ያስቀደመ ድጋፍ አድርጋለች። ሀገራት የራሳቸውን የሥነ-ሕይወት ደህንነት እና የወረርሽኝ መከላከያ አቅም እንዲገነቡ ለመርዳት ፈጣን ድጋፍን፣ ዘመናዊ ምርመራን፣ የጋራ ምርምርን እና ቀጣይነት ያለው ስልጠናን አጣምሮ የያዘ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ - Sputnik አፍሪካ
1/6
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ - Sputnik አፍሪካ
2/6
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ - Sputnik አፍሪካ
3/6
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ - Sputnik አፍሪካ
4/6
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ - Sputnik አፍሪካ
5/6
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የወረርሽኝ ዝግጁነት በተግባር፦ ሩሲያ በጎርጎሮሳዊያኑ በ2025 ለአፍሪካ ያደረገችው ድጋፍ - Sputnik አፍሪካ
6/6
1/6
2/6
3/6
4/6
5/6
6/6
አዳዲስ ዜናዎች
0