የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር 'የክፉዎች ክፉ' ያላቸውን ወንጀለኞች ይፋ ሲያደርግ ዩክሬናውያን ወንጀለኞች በዝርዝሩ አናት ላይ ቁጭ ብለዋል
10:13 27.12.2025 (የተሻሻለ: 10:54 27.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር 'የክፉዎች ክፉ' ያላቸውን ወንጀለኞች ይፋ ሲያደርግ ዩክሬናውያን ወንጀለኞች በዝርዝሩ አናት ላይ ቁጭ ብለዋል
በአሜሪካ ውስጥ በወንጀል የተከሰሱ ከአጠቃላይ 27 ዩክሬናውያን ስደተኞች ከድህረ-ሶቪዬት ሀገራት መካከል "የክፉዎች ክፉ" ወንጀል ዝርዝር ውስጥ ትልቁን ቁጥር መያዛቸውን የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
ሚኒስቴሩ በኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ አስከባሪ በቁጥጥር ስር የዋሉ "የውጭ ሀገር ወንጀለኞች" የሚያሳይ ድረ-ገጽ አዘጋጅቷል፡፡ ይህም ዋሽንግተን በአሁኑ ጊዜ ቅድሚያ ሰጥታ እያባረረች ያለቻቸውን ሰዎች ለሕዝብ ግልጽ የሚያደርግ ነው።
እነዚህ ግለሰቦች በሚከተሉት ወንጀሎች ተከስሰዋል፦
በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣
በፆታ ግንኙነት ወንጀሎች (ሕፃናትን ጨምሮ)፣
በዘረፋ፣
በማጭበርበር እና
በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X



