ከሩሲያ ጋር ያለን ስትራቴጂክ ግንኙነት ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቷል - የኢትዮጵያ አየር ኃይል

ሰብስክራይብ

ከሩሲያ ጋር ያለን ስትራቴጂክ ግንኙነት ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቷል - የኢትዮጵያ አየር ኃይል

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በአየር ኃይል ሙያተኞች ሥልጠና እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በቅርበት እየሠሩ እንደሚገኙ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለከባድ ጥገና ማዕከል ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ሰፊ የሰው ኃይል ወደ ሩሲያ ልከን እያሠለጠንን ነው። ከበፊት ጀምሮም ቴክኖሎጂያቸውን ስንታጠቅ ኖረናል፡፡ ለጥቁር አንበሳ የአየር ትርዒትም ትልቅ አቅማቸውን መላካቸው የዚህ ትብብር አካል ነው" ብለዋል።

በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ ከሚሳተፈው የሩሲያ ልዑክ ጋር ተጨማሪ ስምምነቶች ለመድረስ መታቀዱንም ኃላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0